የአባልነት ግዴታን ስለመወጣት!

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ።

ውድ የዳሩል ኢማን አባላት፥

እንደሚታወሰው በተደጋጋሚ አባላት ያለባቸውን ውዝፍ ወርሃዊ ክፍያና በጠቅላላ ጉባኤ የተወሰኑ ክፍያዎች እንዲከናወን ስናሳስብ መቆየታችን ይታወቃል። በዚህ ወቅት ይህን ተከታታይ ጥሪ እንድንቀርብ ያስገደዱን ዋነኛ ምክንያቶች፤ በመጀመሪያ የሁሉም አባልነት ማረጋገጫና ግዴታ ወርሃዊ ክፍያን መፈፀም ይሆናል። በመቀጠልም ማዕከላችን/መስጅዳችን በግንባታ ፍፃሜ ምዕራፍ እንደመገኘቱ የተለያዩ ቋሚ ወጭዎች ለምሳሌ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ ቆሻሻ ማስወገድ፣ እንሹራንስና የተለያዩ መንግስታዊ ክፍያዎች ቀደም ከተለመደው በጣም ከፍ ብሏል። ይህ በመሆኑ ባለን በጀት ላይ ከፍተኛ ጫና ያመጣ ሲሆን ሊጠናቀቅ የሚገባቸው ጥቃቅን የግንባታና ህጋዊነትን የማረጋገጥ ስራዎች ላይም የበጀት እጥረት ፈጥሮብናል።

ይህንን በመገንዘብ ሁለም አባል ያለበትን ውዝፍ በመክፈል ግዴታውን እንዲወጣና አመራሩም የተሰጠውን አደራ በብቃት እንዲያከናውን እንድታደርጉ በትህትና እንጠይቃለን።

መስጊዳችንን በህብረታችን እንገነባለን!

የዳሩል ኢማን ጀመዐ ስራ አመራር ኮሚቴ

 

26168958_1809883192416416_6520644468327975806_n

.

Message

Darul Iman Ethiopian Muslim Community in Las Vegas, time and again, had done astounding fabulous jobs far and beyond the bounds of its association at numerous times and occasions when people in the society were in dire need of help: at least, for three  funeral expenses of deceased one's, who were a stranger and a non-member of Darul Iman; reasonable economic supports for patients and poverty-stricken ones, and so on; for the very reason that such is the dispensation of the noble cause it stands for.

21192224_1653901694681234_5657564259425660423_n

.

Join / Pay / Donate


ላስ ቬጋስ ውሰጥ ለሚገነባው መስጊድ መረዳት ለምትፈልጉ Donate የሚለውን በመንካት ልትረዱ ትችላላቹሁ ጀዛኩሙላሁ ኸይር::

Your sadaqa is immediately used to for the operational expenses of....
paypal-logo

በzelle ክፍያ ለማከናወን የሚሹ ሁሉ የጀመዐችን አካውንት ይህን መቀበል እንዲችል ተደርጎ የተዘጋጀ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከተውን መረጃ በመጠቀም የተመደበውን መዋጮም ሆነ ወርሃዊ ክፍያ ማከናወን ይቻላል::

Name: Daruliman Ethiopian Muslim community
Email: darulimanlasvegas@gmail.com

zelle logo card_0